Regional Affaires Coordination Directorate
የዳይረክቶሬቱ ዋና ዋና ተግባራት፡
- የፌዴራልና የክልል ኮሚሽኖች ሀገራዊ የሥነምግባር ግንባታና የሙስና መከላከል ስትራቴጂያዊና ዓመታዊ ዕቅድ ማዘጋጀት፣ መከታተል፣ ማስገምገም፣
- አፈፃፀም ሪፖርት ማዘጋጀት ማሳተምና ማሠራጨት፣
- የክልል ኮሚሽኖችን የመፈጸም አቅም ክፍተቶቻቸውን በመለየት የአቅም ማጎልበቻ ሥራዎችን መሥራት፣
- የክልል የፀረ ሙስና ጥምረቶችንና የህብረተሰብ ክፍሎችን እንዲደራጁና እንዲሟሉ፣
- በፀረ ሙስና ትግሉ በንቃትና በትጋት እንዲሳተፉና ሚናቸውን በተገቢው እንዲወጡ ድጋፍ ማድረግ፣
- የተማሪዎች የሥነምግባር ማጎልበቻ ስትራቴጂን እንዲተገበር ክትትል ማድረግ፣
- የክልል ተቋማት የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች እንዲደራጅና የመፈጸም አቅማቸው እንዲጎለብት መደገፍና መከታተል፣
- የሀገሪቱን የፀረ ሙስና ህጎች በክልሎች መከበራቸውን መከታተል፣ መደገፍ፣
- ክልሎች የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ትምህርቶችን/መልዕክቶችን ማዘጋጀታቸውን፣ የህትመት ወጤቶችን፣ የኤሌክትሮኒክና ማህበራዊ ሚዲያዎችን ተጠቅመው ተደራሽ እንዲያደርጉ መደገፍ፣መከታተል
- የተሻለ አፈፃፀም ያስመዝገቡትን በመለየት እንዲበረታቱ ማድረግ፣
- አዳዲስ አሠራሮችን መዘርጋት፣
- የፈፃሚዎችን የመፈጸም አቅም ማሳደግ፣ ክትትል ማድረግ
- የሀገሪቱ የመልካም ሥነምግባር ግንባታና የሙስና መከላከል ሥራን ውጤታማ እንዲሆን ማስቻል ነው፡፡